“ልጅህን በሚሄድበት መንገድ ምራው በሸመገለ ጊዜ ከእርሱ ፈቀቅ አይልም።”[ምሳ.፳፪፥፮]

የህጻናትና ወጣቶች የሰንበት ትምህርት

———-
በሰንበት ትምህርት ቤታችን ከ200 በላይ ተማሪዎችን ስናስተምር መቆየታችን ይታወቃል። ይሁን እንጂ ወቅቱ ያመጣው ፈተና(ኮሮና ቫይረስ) ሳይበግራቸው ከርቀት በዙም(zoom) የሚማሩ ተማሪዎቻችን ቁጥር ውስን ሆኗል። ይህንንም ለመቅረፍ ወላጆች ወሳኙን ሚና ይጫወታሉ። ስለሆነም ወላጆች ልጆቻችሁ ዘወትር እሁድ በተጠቀሰው ሰዓት በዙም ትምህርቱን እንዲከታተሉ በማድረግ ሀላፊነታችንን እንወጣ።

———-
ከተማሪዎች ምን ይጠበቃል?

1.ተማሪዎች በየሳምንቱ የሚሰጧቸውን መጠይቅም ሆነ ጥያቄዎች ተዘጋጅተው መቅረብ አለባቸው።
2.የዙም ካሜራ ክፍት መሆን አለበት።
3.ነጠላ መልበስና መቀመጫ ወንበር ላይ መሆን አለባቸው።
4.የድምጽ ማይክሮፎን በማይናገሩበት ሰዓት ዝግ መሆን አለበት።
5.በክፍል ውስጥ ተሳትፎ ማድረግ ይጠበቅባቸዋል።

———
ከወላጆች ምን ይጠበቃል?
1.ተማሪዎች የተሰጧቸውን የቤት ስራዎች መመልከት እንዲሁም ማገዝ።
2.መጽሐፍ ቅዱስን ተማሪዎች እንዲያነቡ ማበረታታት።

——–
ህጻናትና ወጣቶች ክፍል
ለሌሎች ያጋሩ

የቤተክርስቲያን ተተኪ የሆኑ ልጆቻችንን በማነጽ ሀላፊነታችንን እንወጣ።