ህጻናት እና ወጣቶች/Children &Youth

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ኃይማኖት ደብረ ገነት ቅዱስ አማኑኤል ቤተክርስቲያን የሕጻናትና ወጣቶች የኃይማኖት ሥርዓተ ትምህርት

እንኳን ለዓለም ሁሉ መምሕር ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ እና ቅድስት ወለተ ጴጥሮስ ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን።

††† እንኳን ለዓለም ሁሉ መምሕር ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ እና [...]

By |November 26th, 2020|Categories: Uncategorized|0 Comments

ቅዱስ ፊልዾስ_ሐዋርያ: ኤላውትሮስ እና ለደናግል_አጥራስስ_ወዮና

✞✞✞ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ፡፡ አሜን [...]

By |November 26th, 2020|Categories: ትምህርት|0 Comments

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ኃይማኖት ደብረ ገነት ቅዱስ አማኑኤል ቤተክርስቲያን የሕጻናትና ወጣቶች የኃይማኖት ሥርዓተ ትምህርት መግቢያ፥

መግቢያ

ጥንታዊት፤ ሐዋርያዊት፤ ብሔራዊትና ዓለማቀፋዊት የሆነችው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ተልዕኮዋን ለመወጣትና ቀጣዩን ትውልድ ለማፍራት ልጆቿን በኃይማኖትና በሥነ ምግባር ኮትኩታ ማሳደግ ይጠበቅባታል። ይህንን መንፈሳዊና ማህበራዊ ኃላፊነት ለመወጣት ደግሞ መነሻና ምድረሻ የታወቀ ግልጽ ዓላማና ግቦች ያሉት ሥርዓተ ትምህርት ማዘጋጀት ያስፈልጋል።

የሥርዓተ ትምህርቱ ግቦች በዝርዝር ተለይተው መዘጋጀታቸው የትምህርቱን ይዘት ለመወሰን ከተማሪዎቹ የሚጠበቀው አጠቃላይ ለውጥ(ውጤት) ምን እንደሆነ ከማሳየቱ በተጨማሪ ምን ዓይነት ምዘና ማካሄድ እንደሚያስፈልገው ያስረዳል። በተጨማሪም በነዚህ ግቦች ላይ ተመስርቶ የልጆችን የእድሜና የአእምሮ ብስለት ወይንም የትምህርት ደረጃ ከግንዛቤ በማስገባት ለእያንዳን የትምግርት ክፍል የትምህርት ዓላማዎች መንደፍ ያስችላል።

ይህን ሥርዓተ ትምህርት የደብረ ገነት ቅዱስ አማኑኤል ቤተክርስቲያንን አጠቃላይ ሁኔታ ክግምት ውስጥ በማስገባት የህጻናትና የወጣቶች ሥርዓተ ትምህርት በ 4 ርከን ለመክፈል ተሞክሯል።
ርከን ዕድሜ የት/ ደረጃ

  1. አጸደ ሕፃናት 5 – 6 K

Level Foundation

  1. ቀዳማይ 7 – 10 1 – 4

Level I

  1. ካልአይ 11 – 14 5 – 8

Level II

  1. ሳልሳይ 15 and above 9 – 12

Level III
የሕጻናትና ወጣቶች የኃይማኖት ሥርዓተ ትምህርት አጠቃላይ ግብ።

(Educational Goals)

  1. ልጆች ፈጣሪያቸውን እግዚአብሔርን እንዲውቁና በፍቅሩም እንዲያድጉ ፤
  2. እግዚአብሔር ለሰው ልጅ ያለውን ፍቅር ዓለምን ለማዳን በልጁ በጌታ በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በኩል እንደተገለጠ እንዲያውቁ ማድረግ ፤ (መ.ቅ.)(1)
  3. ልጆች መጽሃፍ ቅዱስ የእግዚአብሔርን ቃል የያዘ ቅዱስ መጽሐፍ እንደሆነ እንዲያውቁ፤
  4. እግዚአብሔር ቃሉን ለሚጠብቁና ፈቃዱን ለሚፈጽሙ የሰጣቸውን የቅድስና ክብር እንዲያውቁ፤ የቅድስና ህይወትንም እንዲለማመዱ ለመስተማር፤ (ክ/ ህይወት)(2)
  5. በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ትምህርተ ኃይማኖት ትውፊት፣ ሥርዓት፣ ባህል፣ በዓላትና የዘመናት አቆጣጠር እንዲያውቁና እንዲጠቀሙበት ለማስተማር፤ (ምስጢራተ ቤ/ን)(የቤ/ን ታሪክ)(ሥነ ፍጥረት)(3)
  6. ልጆች የመንፈሳዊ አገልግሎትን ምንነት ጥቅም እንዲረዱና ሌሎችን አንዲያገለግሉ፤
  7. በሕብረተሰቡ ውስጥ መልካም ሥነምግባር ያላቸው፣ ማኅበረሰባቸውን የሚረዱ ጥሩ ዜጋ ሆነው እንዲያድጉ ለማስቻል፤
  8. ልጆች ከርስቲያናዊ ባልሆኑ ባህሎችና ተጽዕኖዎች የሚመጣውን ግፊት ተቋቁመው በክርስቲያናዊ ሕይወት እንዲኖሩ ለማስቻል፤