COVID -19 | ኮቪድ -19

Dear Brothers and Sisters
I will send you every time when I get information from my Department, the Philadelphia Department of Public Health (PDPH), Center for Disease Control (CDC).  We have a meeting on Thursdays and for Fridays, I will give an update once all division directors meet with the commissioner to update and discuss COVID 19.  “Offer COVID-19 testing to persons of any age who present with new-onset: o Cough o Shortness of breath OR o Two of the following symptoms: fever, chills, muscle pain, sore throat, headache, the new loss of taste or smell”  (this is from the attachment). Ammanuel members are blessed to get information directly from the Health Department.No difference for children or adults for NOW.  I hate when people misinform and send wrong information.  For the city of Philadelphia only the Health Department is responsible for 1.6 million Philadelphians. We need to be careful about what we tell to people.  Now there might be good news that Rite Aid will give COVID 19 tests free of charge.  I will get more information about it. Thanks and stay safe.

 

“Great minds discuss ideas; Average minds discuss events; Small minds discuss people”. Excellence CO.

Kassahun Sellassie, Ph.D., P.E.
Director -Department of Public Health, AMS

 

 ለቤክርስትያናችን አባላት( በአያሌው ጣሰው:ፋርማሲ ዶክተር)

የበሽታው ከፍተኛ ተጠቂዎች /ተጋላጮች፣April 10/2020

1.የበሽታው ምልክቶች፣

የበሽታው ምልክቶች ለቫይረሱ በተጋለጡ ከ2 እስከ 14 ቀን የሚታይ ሲሆን

  • ከፍተኛ ትኩሳት ብርድ ብርድ የሚል ሥሜት ማላብ የጉረሮ መከርከር (መቁሰል)
  • አዲሥ ወይም እያገረሸ የሚሄድ ደረቅ ሣል
  • የትንፋሽ ማጠር
  • ሙሉ ሠውነት ላይ  የህመም (የመቆረጣጠም )ስሜት
  • ትውከት ማቅለሽለሽና ተቅማጥ
  • የማሽተት አቅም ማጣትና
  • የደረት ላይ ውጋት
  • ሌሎችም ሊኖሩ ይችላሉ

 2. የበሽታው ከፍተኛ ተጠቂዎች /ተጋላጮች፣

ሁሉም ሰው ለበሽታው የተጋለጠ ሲሆን በተለየ ሁኔታ ለበሽታው በቀላሉ ሊጋለጡ የሚችሉት ግን

  •  ዕድሜያቸው ከ65 በላይ የሆኑ
  •  የመተንሻ ችግር ያለባቸው ሠዎች (ለምሳሌ የሣምባ
  •  የዐሥም ሕመምተኞች ) እንዲሁም የልብና የስኳር ታማሚዎች
  •  የጉበት የኩላሊት የኤች ዐይ ቪ ታማሚዎች

የሰውነት ዐቅምን የሚያደክሙ መድሀኒቶችን የሚጠቀሙ (የካንሠር ታማሚዎች)

  • ተጓዦች

3. የበሽታው መተላለፊያ መንገዶች፣

  • የበሽታው ዋነኛ መተላለፊያ  መንገድ በሠዎች መካከል በሚደረግ ንክኪ ነው። በግንኙነት ወቅት በሚሠራጨው ትንፋሽ ( በአየር) በማሣል በማሥነጠስ አማካኝነት ነው።

4. የበሽታው መከላከያ መንገዶች፣

  • ስድስት ፊት/ ሁለት የአዋቂ እርምጃ መራራቅ ፣አለመሠባሰብ፣
  • እጅን በደንብ አርጎ በሳሙና መታጠብ፣ሲስሉ ወይም ሲያስነጥሱ ተገቢውን ጥንቃቄ ማድረግ
  • በተደጋጋሚ የሚነኩ ነገሮችን በማፅዳት
  • ራስን ለይቶ ማቆየት
  • የበሽታውን ምልክቶች መከሠት ማሥተዋልና መከታተል ናቸው

5. ከበሽታው መዳናችንን እንዴት እናውቃለን?

  • የበሽታው ምልክቶች ሙሉ በሙሉ ከጠፉ ወይም
  •  ያለምን መድሃኒት ለ72 ሰዐታት ምንም አይነት ትኩሣት ከሌለ

6. የፊት( አፍ ) መሸፈኛ ጥቅምና አጠቃቀም፣


ኮረና ቫይረስ ጥያቄ 4 (April 24/2020)

ጥያቄ: ይህንን የኮረና ቫይረስ በሽታ አስቀድሞ ማወቅ አይቻልም ወይ? በሽታውን ለመለየትና ለማወቅ  እከመጨረሻው ሰዐት ድረስ ለምን ይጠበቃል ? አሁን በቅርቡ ደግሞ በእግር ላይ የሚታይ ምልክት አለው ተብሏል ብታብራሩልን።

መልስ: አዎ በሽታው አዲስ እንደመሆኑ በየሰአቱና በየቀኑ አዳዲስ መረጃዎች ይወጣሉ። ከዚህ አንፃር በሽታውን አስቀድሞ ማወቁን አስቸጋሪ አድርጎታል።

ማብራሪያ: በርግጥየበሽታውን ዋና ዋና ምልክቶች የአሜሪካ የበሽታ መከላከያና መቆጣጠሪያ መሥሪያ ቤት በዝርዝር አስቀምጧል።እነዚህን ምልክቶች ከአሁን በፊት ተመልክተናቸዋል። ሆኖም በሽታው አዲስ እንደመሆኑ በየሰአቱና በየቀኑ አዳዲስ መረጃዎች ይወጣሉ።  በእግር ላይ የሚታይ ምልክት አለው የተባለውም ከዚህ አንፃር ነው። ይህ  በእግር ላይ (በአውራ ጣት ላይ) የሚታይ ምልክት ከኮረና ቫይረስ ጋር ያለው ግንኙነት በስፋት ከተጠና በሁዋላ ወደፊት ሊነገር ይችላል። (ዶ/ር አያሌው ጣሰው)


ጥያቄ: ከራሴ የጤና ጉዳይ በመነሳት የኮረና ቫይረስ ቴስት ማድረግ እፈልጋለው። የኮረና ቫይረስ ቴስት በቀላሉ ማድረግ ይቻላል ? ከተቻለ ቦታው ይነገረን ።ካልተቻለ ለምን?

መልስ: ምርመራውን በቀላሉ ለማግኘት አዳጋች ነው።

ማብራሪያ: አንድ መታወቅ ያለበት ነገር ቢኖር ሁሉም ሰው የመመርመር ግዴታ የለበትም። ማን መመርመር እንዳለበት የአሜሪካ የበሽታ መከላከያና መቆጣጠሪያ መሥሪያ ቤት ዝርዝር መመሪያ አስቀምጧል።  በርግጥ ይህ ትእዛዝ ከግዛት ግዛት ሥለሚለያይ በጥንቃቄ መመልከት ያሻል ። ለማንኛውም የህመም ሥሜት እንደተሰማችሁ የግል ሐኪማችሁ ምን ማድረግ እንዳለባችሁ ተገቢውን ምክር ስለሚሠጣችሁ በቤታችሁ በመቆየትና ሳትውሉ ሳታድሩ ወደ ሐኪማችሁ እንትደውሉ ማሣሠብ እንወዳለን ።በተጨማሪ ወደ ምርመራ ጣቢያዎች ከመሄዳችሁ አስቀድሞ ቀጠሮ መያዝና የሐኪም ማዘዣ እንሚያስፈልግ ከግንዛቤ ውስጥ መግባት አለበት።  በአቅራቢያችሁ  የሚገኘውን የምርመራ ጣቢያ ለማወቅ  የሚከተለውን ሥልክ ቁጥር መደወል ይረዳል (1-877-724-3258)

በአንድ በኩል ቁጥሩ ብዙ የሆነ ታማሚ በመኖሩ በሌላ በኩል ደግሞ ውስን የመመርመሪያ መሣሪያችዎችና ኬሚካሎች በመኖራቸው ምርመራውን በቀላሉ ለማግኘት አዳጋች አድርጎታል ። በመሆኑም ለማን ቅድሚያ ይሠጥ የሚለው ከፍተኛ ቦታ ተሰጥቶታል።

ጠያቂያችን በተለየ ሁኔታ ለበሽታው ተጋላጭ ያደርገኛል የሚያስብላቸው ተጨማሪ የጤና ችግር ካለባቸው ከግል ሐኪማችው ጋር በመነጋገር በግዛቱ ወደተመረጡ የምርመራ ጣቢያዎች በመሄድ ለጥያቄያችው መልስ ሊያገኙ ይችላሉ። (ዶ/ር አያሌው ጣሰው)

 


ከቤተክርስትያን አባላት ስለኮቪድ 19 የቀረቡ ጥያቄዎች (April 17/2020)

ጥያቄ: በኮረና ቫይረስ እንደገና መያዝ ይቻላል?

መልስ: እግርግጠኛ ሆኖ መመለሥ አይቻልም።

ማብራሪያ: ስለዚህ ቫይረስ በየቀኑ አዳዲስ መረጃዎች ይወጣሉ። አዎ ይህ መረጃ በቅርቡ ከወደ ደቡብ ኮርያ ተሰምቷል።

ነፃ ናቸው ከተባሉ በሁዋላ በቫይረሱ በድጋሚ ይያዙ ወይም ቫይረሱ በሰውነታቸው አንቀላፍቶ ወይም ተደብቆ በራሱ መንገድ እንደገና  መንቀሳቀስ(ማገርሸት) ይጀምር በግልፅ አልታወቀም ።የአለም ጤና ድርጅትና ብዙዎች ለጉዳዩ ትኩረት ሰጥተው በመመርመር ላይ ናቸው። ከተመሣሣይ የኮረና ቫይረሶች ያለው ዕውቀት እንደሚያስተምረን በቫይረሱ አንድ ግዜ ከተያዙ (ሰውነታችን ውስጥ ከገባ) ሰውነታችን በራሱ መንገድ መከላከያ እንደሚገነባና ዳግም እንዳንያዝ (እንዳንጋለጥ) ማድረግ እንደሚቻለው ነው። (ለምን ያህል ግዜ በድጋሚ ሳንያዝ እንቆያለን ለሚለው  መልሱ ከቫይረስ ወደ ቫይረስ ይለያያል )

በእርግጥ አንዴ አለብህ አንዴ ደግሞ ነፃ ነህ የመባል ሁኔታ አለ።  ይህ ደግሞ መጀሪያውኑ ሙሉ በሙሉ ከቫይረሱ ነፃ ሣይሆኑ በችኮላ ነፃ ናችሁ ከማለት ፣ከናሙና አወሳሰድ፣ ከሚጠቀሙት ቴክኖሎጂ እና በቤተ ሙከራው ላይ መመሪያዎችን በጥብቅ ተከትሎ ከመሥራትና ከመሣሠሉት ምክንያቶች ጋር ይገናኛል።

በአጭሩ በአሁኑ ሠዐት ይህን ጥያቄ ለመመለስ የሚያስችል የተሟላና በቂ መረጃ የለም።

ውነታውን ለማወቅና ለመለየት ጥናትና ምርምሩ ይቀጥላል።ደግመን ደጋግመን ማስገንዘብ የምንፈልገው ጉዳይ ቢኖር እያንዳንዱ የግሉን ጥንቃቄ በማድግ ራሱንና ሌላውን ይጠብቅ ነው። አካላዊ ርቀታችሁን ጠብቁ፣ እጃችሁን ታጠቡ፣ የአፍ ማፈኛ ተጠቀሙ።የበሽታውን ምልክቶች ነቅችሁ ተከታተሉ።

(በአያሌው ጣሰው :ፋርማሲ ዶክተር)

 

 

 

 

[/fusion_text][/fusion_builder_column][/fusion_builder_row][/fusion_builder_container]